
በመጀመሪያ ለማያውቁ ሰዎች አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወይም አፋብሃ ምንን አንደሚወክልና ከሌሎች ፋኖ አደረጃጀቶች የሚለይበትን ነገሮች ብታስረዳን?
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ: እሺ አመሰግናለው:: ድርጅታችን ከሁሉም በፊት የአማራ ህዝብን ለመጠበቅ እና እኛን ለማዳከም የሚፈልጉ ኃይሎች ከጠላት ጥቃት ለመታደግ የተመሰረተ ድርጅት ነው:: እራሳቺንን ረጅም ታሪክ ያለው ከአያት አባቶቻችን ሲተላለፍ የመጣ የአማራ ተቃውሞ: ለህዝቡ የሚፋለም ንቅናቄ ወራሾች አድርገን ነው ምናየው:: ከሌሎች የ ፋኖ አደረጃጀቶች ምትለዩበት ላልከው ከዋና ተልእኮ አንፃር ልዩነት የለንም:: ሁላችንም የአማራን ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም ቆርጠን የተነሳነን ነን ስለዚህ አፋብሃ አንድነት የሚፈልግ ለአማራ ህዝብ የቆመ ድርጅት ነው::
እሺ አንግዲ አሁን ይሄ ላትጠብቀው ትችላልህ ግን ብዙ ሰዎች አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ጠንከር ያለ ምናልባት ከልክ በላይ የአማራ ብሄርተኝነት የተሞላበት ኃይል ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች መኖር እውነታ ነው:: እንደዚ ለሚሉ ሰዎች ምላሻችሁ ምንድን ነው የ ርዕዮተ ዓለም ፍልስፍናቹህስ ኢትዮጰያኒስት ነን ከሚለው አፋሃድ ጋርስ ምን ልዩነት አለው::
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ:ርዕዮተ ዓለም ፍልስፍናችን የተተከለው የአማራ ህዝብን ጥቅም ከጠላት መከላከል እና ወደፊት በማስቀጠል ላይ ነው:: ለኛ የ አማራ ብሔርተኘት ማለት የሌላው ኢትዮጵያ ህዝብን ፍላጎት ወርውሮ መጣል አይደለም:: በአጭሩ እኛ የአማራ ህዝቦች ከኢትዮጵያ ፖለቲካ አለመገለላቺንን ማረጋገጥ ብቻ ነው:: ተቀዳሚ አላማችን ሕልውናችንን ማስቀጠል ክብር ነፃነትንና የህዝባችን ነፃነት ላይ ተመስረተን ለጠንካራ ኢትዮጵያ ድርሻችንን መወጣት ነው:: አማራ ተዳከመ ማለት ኢትዮጵያ ተዳከመች ማለት ነው:: ስለዚህ ብሄርተኝነታችን ቤታችን የምንገነባበት ጥንቃርያችን ማነነታችንን ማስቀጥያና ወደፊታችንን ማረጋገጫ መሳርያ ነው:: አፋብሃ የተመሰረተበት ሃሳብ ይሄ ነው:: አንዳንድ ሰዎች ውሸት ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ተልኮአችን ላይ ለመፍጠር ይሞክራሉ: ይሄ የፋኖ አደረጃጀቶችንም ይጨምራል:: አፋሃድ ማለቴ አይደለም ሌሎች ትንንሽ የፋኖ ቡድኖች ራሳቸውን ኢትዮጵያኒስት ነን ብለው የሚጠሩትን እንጂ:: ሌሎችም አሉ ከ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ለመስራት ፍቃደኛ ሆነው የአማራን ህዝብ ነፃ እናወጣለን የሚሉ በርግጥ ሁላችንም አየተዋጋን ያለው ለዢው አላማ ነው:: ነገር ግን የአማራ ፋኖ ንቅናቄን በሚገባ ይገልፀዋል ይዎክለዋል ብዬ የማምነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ነው:: ጠንካራ አመራሮች ብትል የህዝብ ድጋፍ ብትል ከማይሰበር ወኔ ጋር አጣምረን የ ማይቀረውን ድል አሳክተን የ ዘር ጭፍጨፋውን አስቁመን አማራን ድጋሚ በ ፖለቲካው ሰሌዳ ላይ ለሃምሳ ዓመት የተገለልንበት ሰሌዳ ላይ መልሰን አናስገባዋለን:: ልጨምር ምፈልገው ነገር ቢኖር አንዳንድ ከራሳችን ከአማራ ወተው በ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት አንዳይሳካ የሚያደርጉ ከፋፋይ አስተያየት የሚሰጡ አንተንም ጨምሮ ማለት ነው ልመክራችሁ ምፈልገው ነገር ቢኖር ራሳችሁን የ ፋኖ ቡድኖች ግጭት ምክንያት ከመሆን አንድትታቀቡ ነው::
በጣም አሪፍ አሁን ባልከው ነገር ላይ በጥልቅ መግባት እፈልግ ነበር ግን በቂ ጊዜ ስለሌን ወደቀጣዩ ጉዳይ እንግባ:: አፋብሃ በቅርቡ ሰሜን ወሎ መከላከያ ላይ ጥቃት ፈፅሟል:: በአጭሩ ምን አንደተካሄደ ብታስረዳን?
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ:የደቡብ ወሎው ድል እጅግ በጣም ወሳኝ ድል ነው ለኛ:: ወሳኝ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ሲገፋ የነበረውን የ መከላከያን ጦር ተጋጣሚዎቻችን ገፍተን በማስወጣት መሬት ላይ ቁልፍና ስትራቴጂክ ቦታዎችን ነፃ ማስወጣት ችለዋል:: ይሄ ድል ሊሳካ የቻለው ለጫና አንገት ማይደፋው የዎሎ ሕዝብ የታጠቀው ወኔ አይበገሬነት ነው:: መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ደጋግሞ እንድሚለው ነው የአሳምነው ልጆች መንፈስ የማይሰበሩ የወሎ ፋኖዎች በዚ ኦፕሬሽን አንድ ሆነን ከተነሳን ማይቻል ነገር እንደሌለ በሚገባ አሳይተውናል ደስም ብሎናል::
እናንተ የምትመሩት ይሄ የአፋብሃ ክንፍ በምዕራብ ጎጃም የሚንቀሳቀሰው በዚ በወልዲያው ጥቃት ተጠቃሚ ባይሆንም ግን ምን አይነት ስትራቴጂክ ጥቅም ለአፋብሃ እንደ አንድ ድርጅት ያገኛል ብለህ ታስባለህ በተጨማሪም እንደዚ አይነት ግዛታዊ ድል ብዙም ጥክም አያመጣም: ከመልቀአ ምድራዊ አቀማመጡ አንፃር ብዙም ፋይዳ የለውም ለሚሉ ተቺዎች ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ?
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ:ከአቀማመጡ አንፃር የሚነሱ ቅረታዎች ያው ትንሽ እውነታ አላቸው ምክንያቱም ሰሜን ወሎ ብዙም ከ ወሳኝ የ መንግስት ተቋማት ወይም የጦር ካምፖች ብዙም ቅርበት ስሌለው ብሎም ደግሞ ከገዢው ኃይል መቀመጫ አራት ኪሎና ከሌሎች የ አማራ ክልል ግዛቶች አንፃር የራቀ ስለሆነ ተቺቶች እውነትም ትንሽ መሰረት አላቸው ነገር ግን ድሉ አጅግ ወሳኝ መሆኑ የተገኙ የጦር መሳርያ: ምርኮኛ እና ሌላው ቢቀር የማሸነፍ መስንፈስ ይዞ የመጣ መሆኑን ማንም ይመሰክራል ሌላው ቢቀር መነቃቃት እና ግስጋሴ ይዞ የሚመጣ መነሳሻ ስለሆነ በትልቁ መከበር ያለበት እንደሆነ አምናለው:: አይተህ ከሆነ መላው የአማራ ክልል ላይ መነቃቃት ተፈጥሯል ለረጅም ጊዜ አላየነውም ነበር ይህን መነቃቃት:: መጠቆም ያለብኝ ሌላው ነገር ደሞ የአፋብሃ ጥምረት ጓዶቻችን በ ምሬ ወዳጆች ሚመራው የ ምስራቅ ፋኖ በዚ አረመኔ ስርዓት ሲሰቃይ የከረሙትን እነዚ የአማራ ቦታዎች ነፃ በማውጣቱ ትልቅ ክብር ይገባቸዋል:: ትግሉ ላይ ልዩነት ለማምጣት በአብሮነት መነሳት በቂ አንደሆነ አሳይተዋል እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አፈልጋለው በዚ አጋጣሚ
ከመንግስት የመልሶ ማጥቃት ይጠበቃል ወይ እናንተም ደሞ አንደ አንድ ፖለቲካ ቡድን ምን ትጠብቃላችሁ ከዚ ክስተት በሁአላ?
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ:በሚገባ:: መንግስት ለመምታት አንደምሞክር በሚገባ እንጠብቃለን ከዚ በፊት ባሉን ልምዶችም ተመስርተን በቂ ዝግጅትም አድርገናል:: ዝግጁ ሆነንን በመጠበቅ: ማህበረሰባችን ራሱን ለመከላከል አንዲችል ዝግጁነት ላይ አተኩረን አየሰራን የ ህዝቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ እንሞክራለን:: ተቀዳሚ መደረግ ያለባቸው የንፁሃን ሰፈሮች: ትምርት ቤቶችና: ጤና ጣቢያዎች ናቸው:: አገዛዙ ግድ የለሽና የአማራ ሕዝብ ጠላት እንደመሆኑ አነዚህ መሰረታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አያጠቁም ብሎ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል:: ከዚ ቀደም በተደጋጋሚ ተመልክተነዋል: ድሎችን ተከትሎ ጠንከር ያለ የመልስ ምት ለመሰንዘር የመሞከር ህዝብን የማስፈራራት መደጋገም በቅርብ ጊዜያት ታይተዋል:: ያው እንዳልኩህ ነው ንፁሃን አማራዎችን ከዚ ዘር አጥፊ ጥቃት ለመከላከል የተቻለውን ያህል ጥረት ይደረጋል::
በቅርቡ አፋብሃ አና አፋሃድ መካከል አብሮ መስራት ጥምር ጥቃቶች አና አጠቃላይ የተሻለ መግባባት የሚታይ ይመስላል የተዋሃደ አንድ ወጥ የአማራ ግንባር ምናይበት ጊዜ ደርሷል ወይስ የርዕዮተ ዓለም ፍልስፍናችሁ ሰፊ ልይነት አንድነቱን ለማሳካት አንቅፋት ይሆናል
ሀብታሙ የሱፍ ክንዴ:አዎ መቶ ፐርሰንት:: በሚገባ አንድ የአማራ አደረጃጀት ማሳካት የሚቻል እውነት ለመናገርም ደሞ ከቀን አንድ ትግሉ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ይህንን ለማሳካት ስንሰራ ነበር:: በርግጥ ልዩነቶች አሉ እሱን መካድ አይቻልም ሆኖም መነሻቸው ግለሰባዊ አለመተማመን ጠቦች አለመግባባቶች ናቸው ግለሰባዊ ሚለውን አስምርበት: አላማችን የተለያየ ሆኖ አይደለም:: ማንኛውም ቡድን አፋብሃ በለው አፋሃድ በለው ወይም ሌሎች ትናናሽ ፋኖ አወቃቀሮች ሁሉም ለተመሳሳይ ግብ ነው ጠመንጃ ያነሳነው አሱም የአማራ መሬትና ህዝብ መከላከል ብሎም ክብራችንን ማስመለስ ነው:: ችግሩ ጥምረትና መግባባት እንጂ አላማ ሆኖ አያውቅም ወደፊትም አይሆንም
በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሰው አንደሚያውቀው በተለያየ ደረጃ ንግግግሮች ተጀምረዋል:: ወታደራዊ መሪዎች: ፖለቲካዊ አመራሮች: አባቶች አና ሌሎች ተወካዮች እነዚ ድርድሮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ ነው:: ቀላል አይደሉም ግን እድገት መሻሻል እየታየ ነው:: በብዙ ቦታዎች በተለይ ሰሜን እና ምስራቅ አማራ የትብብር ተግባራዊ ትብብር አይተናል የሚበረታታ ነው:: ከስህተቶች ለመማርም እድል ይሰጣል ምክንያቱም አለመግባባት አለመነጋገር ለ ስርዓቱ ብቻ ነው ምተክመው:: ግንባር ላይ ያሉ ጓዶች ይሄ ሰልችቷቸዋል አንድ ወጥ የአማራ ድርጅት ይፈልጋሉ አንድ የ ህዝቡን ድምፅ የሚዎክል:: እናም ይመስለኛል ነገሮች ወደዛ ነው አየሄዱ ያሉት ቀስ በቀስ:: ነገሩ ግልፅ ነው አንድነት ማለት ሃሳቦች ወይም ማንነትን መተው አይደለም ትግሉን ከግል ጥክም ማስቀደም ነው ይሳካል እንደ ፈጣሪ ፈቃድ::